Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1781

Artist Yehunie Belay “ሰላምሽ ይብዛ” New single music Released: June 21, 2018

$
0
0

ተወዳጁ የባህል ሙዚቃ ድምፃዊ አርቲስት ይሁኔ በላይ “ሰላምሽ ይብዛ” የሚል አዲስ ነጠላ ዜማ እንደሚለቅ በትላንትናው ዕለት መዘገባችን ይታወሳል ። በዚህም መሰረት ዛሬ የተለቀቀውን ነጠላ ዜማ በዩቲዩብ ላይ የተጫነ ሲሆን ከታች ሊንኩን ተጭነው ያገኙታል።

አርቲስቱ በቅርብ ስራዎቹ(ሰከን በል፣ ጣና  እና  እንዳትውል ተክፍተህ” በሚሉ ዜማዎቹ )ከፍተኛ ተደማጭነት እንደነበራቸው እናስታውሳናል። ”ሰከን በል’ የተሰኘ  ዜማው በ2008 ዓም በአማራ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል በነበረ ህዝባዊ አመፅ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች አጋርነቱን ለመግለፅ የለቀቀው የቁርጥ ቀን ልጅ መሆኑን እናስታውሳለን።

ከዚህም በተጨማሪ በጣና ሀይቅ ላይ የደረሰውን የእንቦጭ አረም ለመከላከል የሚረዳ ወገኑን ለማስተባበር የሚውል ”ጣና“ የተሰኘ ነጠላ ዜማ በመልቀቅ በድጋሚ አስደምሞናል። እንዲሁም ይህን ዜማውን በተለያዩ የአሚሪካ ከተሞች በተደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ መድረኮች በመገኝት የወገን እና የሀገር ተቆርቋሪነቱን አሳይቷል።

በመጨረሻም “ሰላምሽ ይብዛ” የሚለውን አዲሱን የአርቲስት ይሁኔ በላይ ሙዚቃ ተጋበዙልን ፡

 

The post Artist Yehunie Belay “ሰላምሽ ይብዛ” New single music Released: June 21, 2018 appeared first on Bawza NewsPaper.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1781

Trending Articles