Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1781

Artist Yehunie Belay coming back again with a new single song “ሰላምሽ ይብዛ”: coming soon

$
0
0

ተወዳጁ የባህል ሙዚቃ ድምፃዊ አርቲስት ይሁኔ በላይ  አዲስ ነጠላ ዜማ እንደሚለቅ የደረሰን መራጃ ያሳያል። የሙዚቃው መጠሪያው “ሰላምሽ ይብዛ” አገራዊ ሙዚቃ ሲሆን በመጭዎቹ ሁለት ቀናት እንደሚለቀቅ ተረድተናል። በስልክ ጠይቀን እንዳረጋገጥነው ስቲዲዮ እንደገባና ሙዚቃውን በቶሎ ለማድረስ ሌት እና ቀን እየሰራ እንደሆነ ለባውዛ ዝግጅት ክፍል ገልፆልናል።

አርቲስቱ በቅርብ ስራዎቹ(ሰከን በል፣ ጣና  እና  እንዳትውል ተክፍተህ” በሚሉ ዜማዎቹ )ከፍተኛ ተደማጭነት እንደነበራቸው እናስታውሳናል። ”ሰከን በል’ የተሰኘ  ዜማው በ2008 ዓም በአማራ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል በነበረ ህዝባዊ አመፅ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች አጋርነቱን ለመግለፅ የለቀቀው የቁርጥ ቀን ልጅ መሆኑን እናስታውሳለን።

ከዚህም በተጨማሪ በጣና ሀይቅ ላይ የደረሰውን የእንቦጭ አረም ለመከላከል የሚረዳ ወገኑን ለማስተባበር የሚውል ”ጣና“ የተሰኘ ነጠላ ዜማ በመልቀቅ በድጋሚ አስደምሞናል። እንዲሁም ይህን ዜማውን በተለያዩ የአሚሪካ ከተሞች በተደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ መድረኮች በመገኝት የወገን እና የሀገር ተቆርቋሪነቱን አሳይቷል።

ለማንኛውም አዲሱን ነጠላ ዜማ “ሰላምሽ ይብዛ” እንደደረሰን የምናስደምጣችሁ መሆኑን ቃል እንገባለን።

 

The post Artist Yehunie Belay coming back again with a new single song “ሰላምሽ ይብዛ”: coming soon appeared first on Bawza NewsPaper.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1781

Trending Articles