እነዚህ ምልክቶች ሰዎች በቀላሉ ሊያልፏቸው የማይገቡ እና ጤና ላይ ቸግር እንዳለ የሚያሳዩ ምልክቶች ናቸው። በመሆኑ በዝርዝር የቀረቡት ጉዳዮች በቀላሉ የማይታለፉ የጤና እክሎች በመሆናቸው ምልክቶቹ ሲታዩ ወደ ህክምና ተቋማት ማምረት ያስፈልጋል ተብሏል።
1.በእጅና እግር ላይ የሚከሰት የድካም ስሜት
ሰዎች የጤና እክል እንዳጋጠማቸው ከሚያሳዩ ምልክቶች መካከል በእጅ ፣እግር እና ፊት ላይ የሚከሰት የድካም ስሜት ነው።
በእነዚህ የአካል ክፍሎች የሚከሰተው የድካም ስሜት ሰዎች ለስትሮክ መጋለጣቸውን የሚያሳይ ምልክት ሊሆን ይችላል።
ይህ ምልክት በአንደኛው የሰውነት ክፍል ሊያጋጥም የሚችለውን ስትሮክ የሚያሳይ ነው ተብሏል።
እንዲሁም የእራስን ሚዛን መቆጣጠር አለመቻል፣ ማዞር እና በአግባቡ መራመድ አለማቻል የስትሮክ ምልክት እንደሆነ ተጠቁሟል።
በመሆኑም ሰዎች በአካላቸው ላይ እንደዚህ አይነት ምልክትን ሲታዘቡ ፈጥነው ወደ ህክምና ተቋም ማምራት ይጠበቅባቸዋል።
2.በደረት ላይ የህመም ስሜት ሲኖር
የህክምና ባለሙያዎች እንደሚናገሩተ የደረት ህመም በእንቅስቃሴና ንቁ በሆኑ ጊዜና ወቅት የሚከሰት ከሆነ ለልብ በሽታ፣ ልብ ድካም እና ለሌሎች ተያያዥ የልብ
ችግሮች ምልክት ስለሆነ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል።
ደረት ላይ የመክበድና የመወጣጠር ስሜት ከተወሰኑ ዲቂቃዎች ኋላ የሚጥል ከሆነ የህክምና እርዳታ ማግኘት ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።
3.ባት ላይ ያለ የህመም ስሜት
ሰዎች ለጤናቸው ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው እና ጤናቸው እክል እንዳጋጠመው ከሚጠቁሙ ምልክቶች መካከል ባት ላይ የሚከሰት ህመም አንዱ ነው።
ይህ ባት ላይ የሚከሰት ህመም በእግር ላይ የደም መርጋት እንዲከሰት የሚያሳይ እንደሆነ ተገልጿል።
የባት ህመም የሚከሰተው ረጅም ሰዓት በመቀመጥ ፣ በህመም ምክንያት ለረጅም ጊዜ በመተኛት እና በተለያዩ ምክንያቶች እንደሚከሰት ተጠቁሟል ።
ሰዎች ሲራመዱ አና ሲቆሙ የህመመ ስሜት የሚሰማቸው ከሆነ ችግሩ የደም መርጋት ነው ተብሏል።
4. ደም የተቀላቀለበት ሽንት
የተለያዩ ምክንያቶች የሰዎች ሽንት ደም የተቀላቀለበተ እንደሚሆን ባለሙያዎች ይናገራሉ።
የሰዎች ሽንት ደም የተቀላቀለበት ሲሆን፥ በውስጥ የሰውነት ክፍላቸው እና በጀርባቸው የህመም ስሜት ይፈጠራል።
ከዚህ ባለፈ ችግሩ የኩላሊት ጠጠር በሰውነት እንደተከሰተ የሚያሳይ ነው ተብሏል።
እነዚህ የኩላሊት ጠጠሮች ሰዎች በሚሸኑበት ወቅት በሰውነት ላይ የሚዘዋወር በመሆኑ ከፍተኛ የህመም ስሜትን ይፈጥራል።
ይህ ደም የተቀላቀለበተ ሽንት ሰዎች በተደጋጋሚ ወደ መፀዳጃ ቤት እንዲመላለሱ የሚያደርግ መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን፥ የዚህ አይነት ችግር ሲያጋጥም ጊዜ ሳይወስዱ ወደ ህክምና ተቅቋም መሄድ ያስፈልጋል።
5.የአተነፋፈስ ችግር
የአተነፋፈስ ችግር በህክምና በቀላሉ ማከም የሚቻል እንደሆነ ነው የሚገረው በመሆኑም ሰዎች በሚተነፍሱበት ወቅት ድምፅ የሚያወጡ ከሆነ ወደ ህክምና ተቋማት ማምራት ይጠበቅባቸዋለ።
ይህን የአተነፋፈስ ችግር በቀላሉ እና በፍጥነት ካልተቀረፈ ጉዳቱ ክፍተኛ ሊሆን ይችላል ተብሏል።
6 እራስ ለማጥፋት ማሰብ
ሰዎች በህይወታቸው ተስፋ ሲቆርጡ እና ለመኖር ምንም ምክንያት እንደሌላቸው ማሰብ ከጀመሩ በፍጥነት ይህን የአመለካከት ችግራቸውን መቅረፍ እንዲችሉ ስነ ልቦና ባለሙያዎችን እንዲያገኙ ይመከራል።
ምንጭ፥ Fana
The post Signs & Symptoms which tells about your Health problem(ጤና ላይ ችግር እንዳለ የሚያሳዩ ምልክቶች) appeared first on Bawza NewsPaper.